ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ - ከቸርቻሪ ወደ ግዙፍና ዘመናዊ የሃንዳይ መኪናዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተሻግሯል
ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ እጅግ በጣም ዘመናዊና ግዙፍ በሆነው የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ውስጥ የሃንዳይ መኪናዎችን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚገጥም ሲሆን በዚሁም ፋብሪካ ውስጥ የኤሌክትሪክ መኪናዎችም እንደሚገጣጠሙ ሲያሳውቅ በደስታ ነው፡፡ ኩባንያችን ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ ሁሌም በሚተገብረው የሁል ጊዜ መሪ ሀሳብ ‘’አዲስ አስተሳስብ አዲስ አማራጮች’’ነው::
ኩባንያችን ከአስር አመት በፊት ያስቀመጠውን ራዕይ ህልም ሆኖ ሳይቀር ዛሬ ላይ እውን አድርጎታል፡፡ ይህም የሆነው በዚህ አስር አመት ውስጥ አብረውን በተጓዙት ስትራቴጂክ አጋሮቻችን ነው፡፡ ለሚቀጥለውም 10 አመት አዲስ ራዕይ በማስቀመጥ ላቅ ያለ ስኬትን ከአጋሮቹጋ በማሳካት ለአገራችንም የሚጠበቅበትን ሁለንተናዊ አስተዋፆ እያበረከተ ይጓዛል፡፡
ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ ሁሉንም አጋሮቹን እንኳን ደስ አላችሁ እያለ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናውን በማቅረብ ለወደፊትም ይበልጥ በመስራት በስኬት እንደሚቀጥል ሙሉ እምነቱ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን በዚሁ ድህረገጽ የምናስተላልፍ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
መልካሙ አሰፋ
ዋና ስራ አስፈፃሚና ማኔጂንግ ዳይሬክተር
አድራሻ፡ ከዋናው መስሪያ ቤት ከሳሪስ 15ኪሜ ርቀት ላይ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ
Facebook comments error!
Facebook app ID is required to use Facebook comments. Please ensure you have specify a valid Facebook app ID.