ሀሰተኛ የሶሻል ሚዲያ ወሬ ድርጅታችንን በተመለከተ

ከህዳር 3፣2011 ዓ.ም ጀምሮ ከስራው ታግዷል ምርምራ እየተደረገበት ነው የሚሉ ወሬዎች በሶሻል ሚዲያ ማለትም በፌስ ቡክ እየተሰራጨ ይገኛል ይህም ከእውነት የራቀ መሆኑን ኩባንያችን ምንም አይነት እገዳና ምርምራ ላይ እንዳልሆነ ለአጠቃላይ ህብረተሰቡ እና በዋነኝነት ለክቡራን ደንበኞቻችን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ኩባንያችን ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ ላለፉት በርካታ አመታት ለአገራችን መልክአ ምድርና አየር ንብረት ተስማሚ የሆኑትን የሃንዳይ ደቡብ ኮሪያ ስሪት መኪናዎች እና ኦሪጅናል መለዋወጫ እቃዎችን ብቻ በማስመጣት ለገበያ እንደሚያቀርብ ይታወቃል፡፡ በቅርቡም  እጅግ ዘመናዊ ፤ግዙፍ እና ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በመመደብ ገንብቶ ያጠናቀቀውን የመኪና መገጣጠሚያ ፍብሪካ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚያስመርቅ እና ለአገራችንም የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ሲያበስር  ላቅ ባለ ደስታ ነው፡፡

ከህዳር 3፣2011 ዓ.ም ጀምሮ  ከስራው ታግዷል ምርምራ እየተደረገበት ነው የሚሉ ወሬዎች በሶሻል ሚዲያ ማለትም በፌስ ቡክ እየተሰራጨ ይገኛል ይህም ከእውነት የራቀ መሆኑን ኩባንያችን ምንም አይነት እገዳና ምርምራ ላይ እንዳልሆነ ለአጠቃላይ ህብረተሰቡ እና በዋነኝነት ለክቡራን ደንበኞቻችን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ኩባንያችን ከመቼውም ጊዜ  በላይ ጠንክሮ እየሰራ እና የአገልግሎት አድማሱን እያሰፋ ለአገርም ጉልህ አስተዋጾ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ኩባንያችን ሁሌም እንደሚለው አዲስ አስተሳሰብ አዲስ አማራጭ መርህ በመከተል ለክቡራን ደንበኞቹ እና ለሌሎች አጋሮቹ የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን  የሚጠበቅበትን አገልግሎት ለመስጠት ከምን ጊዜም በላይ ዝግጁ ነው ፡፡

ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ

ህዳር 04,2011

News and Events