- Details
- Hits: 4261
ለክቡራን ደንበኞቻችን ከድህረ ሽያጭ ክፍል የተሰጠ መረጃ
የጥገና ማዕከላችን በሰለጠኑ ባለሙያዎች በዘመናዊ የጥገናና የምርመራ መሳሪያዎች በመታገዝ የተሻለና ጥራት ያለው የአምራች ኩባንያውን የጥገና ደረጃ በጠበቀ መልኩ አገልግልዎት ይሰጥዎታል፡፡
የጥገና ማዕከላችን ተሸከርካሪዎ የሚያስፈልገውን ማንኛውም አይነት ጥገና የምንሰጥ ሲሆን ከዚህም ዋና ዋናዎቹ፡
- መደበኛ ሰርቪስ
- የትራንስሚሽን ጥገና
- የሞተር ጥገና
- የኤሌክትሪክ ጥገና
- በኮምፒውተር የተገዘ አጠቃላይ ምርመራና ጥገና
- የአካል ጥገና
- የአካል ቀለም ቅብ ስራ (በዘመናዊ የቀለም መቀመሚያና መቀቢያ መሳሪያ የታገዘ የቀለም ቅብ ሸራ)
ከድርጅታችን ተሸከርካሪ ሲገዙ በጥገና ክፍሉ በኩል የሚያገኙት ጥቅም
- የመጀመሪያ 1,000 ኪ.ሜ ነፃ ምርመራ ያገኛሉ
- የመጀመሪያ 5,000 ኪ.ሜ የጉልበት ዋጋ ሳይከፍሉ አገልግሎት ያገኛሉ
- በሁሉም የሰርቪስ አገልግሎቶች ከሚቀየሩት የመለዋወጫ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ ያገኛሉ
- ለተሽከርካሪዎ የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ
- መኪናዎ የሚያስፈልገውን ወቅታዊ ጥገና ሁሉንም በተከታታይ በጥገና ማዕከላችን የሚከታተሉ ከሆነና ተሸከርካሪዎን መቀየር/መሸጥ በሚፈልጉበት ወቅት የመኪናዎን ታሪክ የሚገልጽ የምስክር ወረቀት እና ነፃ የፍተሻ አገልግሎት ያገኛሉ
- በድርጅታችን በኩል የገዟቸው ተሸከርካሪዎች በምርት ወቅት የተፈጠሩ ችግሮች ሲያጋጥምዎ በአምራች ኩባንያው የተሰጠ የ50,000 ኪ.ሜ እና የሁለት አመት ዋስትና የገኛሉ
መኪናዎ በአምራች ኩባንያው ፈቃድ ባለው የጥገና ማዕከል በማስገባትዎ የሚያገኙት ጥቅም
- በአምራች ኩባንያው የተመረቱና ጥራታቸው የተጠበቀ መለዋወጫ ለመኪናዎ ይቀየራል
- ለመኪናዎ የሚያስፈልጉት የመለዋወጫ እቃዎች በትክክል ስለመቀየሩ እርግጠኛ ይሆናሉ የተቀየሩትንም እቃዎች ይረከባሉ
- መኪናዎ ለሚገጥመው ችግር ከአምራች ኩባንያው በመጣ ዘመናዊና ኮምፒውተራይዝድ የመመርመሪያ መሳሪያ በመታገዝ የጥገና አገልግሎት ያገኛሉ
- መኪናዎ ላይ ለተከናወነው ጥገና ሙሉ ዋስትና ያገኛሉ
- መኪናዎ በድርጅታችን የጥገና ማዕከል ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ስራው እስኪጠናቀቅ ሙሉ የመድን ዋስትና ይኖረዋል
- ከሁሉም በላይ ግን ይህን ትልቅ ንብረትዎ የሆነውን ተሸከርካሪዎን በአምራች ኩባንያው የጥገና መመሪያ መሰረት ከተከታተሉና ካስጠገኑ ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት ከአደጋ መጠበቅዎና ንብረትዎንም ላሰቡት ጊዜ በአግባቡ መጠቀም እንደሚችሉ አይዘንጉ